2 ዜና መዋዕል 4:1-6 NASV

1 ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱ ዐሥር ክንድ የሆነ የናስ መሠዊያ ሠራ።

2 እንዲሁም የጐኑ ስፋት ከጠርዝ እስከ ጠርዝ ዐሥር ክንድ፣ ቁመቱ አምስት ክንድ የሆነ ክብ በርሜል ቀልጦ ከፈሰሰ ብረት ሠራ፤ ዙሪያውም ሲለካ ሠላሳ ክንድ ሆነ።

3 ከበርሜሉ ከንፈር በታችም በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት ላይ ዙሪያውን ዐሥር የኮርማ ቅርጾች ነበሩበት፤ ኮርማዎቹም ከበርሜሉ ጋር አንድ ወጥ ሆነው በሁለት ረድፍ ቀልጠው ተሠርተው ነበር።

4 በርሜሉ በዐሥራ ሁለት ኮርማዎች ላይ የቆመ ሲሆን፣ ኮርማዎቹም ሦስቱ ወደ ሰሜን፣ ሦስቱ ወደ ምዕራብ፣ ሦስቱ ወደ ደቡብ፣ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ ይመለከቱ ነበር። በርሜሉ በእነዚህ ላይ ያረፈ ሲሆን፣ የሁሉም ጀርባ ወደ መካከል የዞረ ነበር።

5 የበርሜሉ ውፍረት አንድ ስንዝር፣ ከንፈሩ ደግሞ የጽዋ ከንፈር ወይም የሱፍ አበባ ይመስል ነበር፤ ይህም ሦስት ሺህ የባዶስ መስፈሪያ የሚይዝ ነበር።

6 እንዲሁም ዐሥር የመታጠቢያ ገንዳዎች አሠርቶ አምስቱን በደቡብ፣ አምስቱን ደግሞ በሰሜን በኩል አስቀመጠ፤ ገንዳዎች ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርቡት ነገሮች የሚታጠቡባቸው ሲሆኑ፣ በርሜሉ ግን ለካህናት መታጠቢያ የሚያገለግል ነበር።