12 ሁለቱ ዐምዶች፣በአዕማዱ ጫፍ ላይ ያሉት ሁለት ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት የሚያስጌጡ ሁለት ዙር መርበቦች፤
13 በዐምዶቹ ላይ ያሉትን ሁለቱን፣ ባለ ሳሕን ቅርጽ ጒልላት እንዲያስጌጡ ለያንዳንዱ መርበብ ሁለት ዙር ሮማኖች ለሁለቱም ዙር መርበቦች በድምሩ አራት መቶ ሮማኖች፤
14 መቆሚያዎች ከነመታጠቢያ ሳሕኖቻቸው፤
15 በርሜሉና እርሱን የተሸከሙት ዐሥራ ሁለት ኮርማዎች፤
16 ምንቸቶችና መጫሪያዎች፣ሜንጦዎችና ከነዚሁም ጋር የተያያዙ ዕቃዎች።ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆን ለሰሎሞን የሠራቸው ዕቃዎች በሙሉ ከተወለወለ ናስ የተሠሩ ነበሩ።
17 ንጉሡም እነዚህ ዕቃዎች በዮርዳኖስ ሸለቆ፣ በሱኮትና በጽሬዳ መካከል ባለው በሸክላ ዐፈር ቦታ ቀልጠው በሸክላ ቅርጽ ተሠርተው እንዲወጡ አደረገ።
18 እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደሆነ አልታወቀም ነበር።