ሆሴዕ 10:5-11 NASV

5 በሰማርያ የሚኖረው ሕዝብ፣በቤትአዌን ስላለው የጥጃ ጣዖት ይፈራል፤ሕዝቡም ያለቅስለታል፤በክብሩ እጅግ ደስ ያላቸው ሁሉ፣አመንዝራ ካህናትም እንደዚሁ ያለቅሱለታል፤በምርኮ ከእነርሱ ተወስዶአልና።

6 ለታላቁ ንጉሥ እንደ እጅ መንሻ፣ወደ አሦር ይወሰዳል፤ኤፍሬም ይዋረዳል፤እስራኤልም ስለ ጣዖቱ ያፍራል።

7 ሰማርያና ንጉሥዋ፣በውሃ ላይ እንዳለ ኩበት ተንሳፍፈው ይጠፋሉ።

8 የእስራኤል ኀጢአት የሆነው፣የአዌን ማምለኪያ ኰረብታ ይጠፋል፤እሾኽና አሜኬላ ይበቅልባቸዋል፤መሠዊያዎቻቸውንም ይወርሳል፤በዚያን ጊዜ ተራሮችን፣ “ሸፍኑን!”ኰረብታዎችንም፣ “ውደቁብን!” ይላሉ።

9 “እስራኤል ሆይ፤ ከጊብዓ ጊዜ ጀምሮ ኀጢአት ሠራችሁ፤በዚያም ጸናችሁ፤በጊብዓ የነበሩትን ክፉ አድራጊዎች፣ጦርነት አልጨረሳቸውምን?

10 በፈለግሁ ጊዜ እቀጣቸዋለሁ፤ስለ ድርብ ኀጢአታችሁም ይቀጧቸው ዘንድ፣በእነርሱ ላይ ይሰበሰባሉ፤

11 ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድ፣እንደ ተገራች ጊደር ነው፤በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ቀንበርን አኖራለሁ፤ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ይሁዳ ያርሳል፤ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል።