6 ጠዋት ላይ ዘርህን ዝራ፤ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ይህ ወይም ያ፣ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።
7 ብርሃን መልካም ነው፤ፀሓይንም ማየት ለዐይን ደስ ያሰኛል።
8 ሰው ምንም ያህል ብዙ ዓመት ቢኖር፣በእነዚህ ሁሉ ይደሰት፤ነገር ግን ጨለማዎቹንም ቀናት ያስብ፤እነርሱ ይበዛሉና፤የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
9 አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤የልብህን መንገድ፣ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።