2 ፀሓይና ብርሃን፣ጨረቃና ከዋክብት ሳይጨልሙ፣ደመናትም ከዝናብ በኋላ ሳይመለሱ፣
3 ቤት ጠባቂዎች ሲርዱ፣ብርቱዎች ሲጐብጡ፣ጥቂት በመሆናቸው ፈጪታዎች ሲያቆሙ፣በመስኮት የሚያዩትም ሲፈዙ፣
4 ወደ አደባባይ የሚያወጡ በሮች ሲዘጉ፣ወፍጮ ሟልጦ ድምፁ ሲላሽ፣ሰው በወፍ ድምፅ ሲነሣ፣ዝማሬው ሁሉ ሲዳከም፤
5 ዳገት መውጣት ሲያርድ፣መንገድም ሲያስፈራ፣የለውዝ ዛፍ ሲያብብ፣አንበጣም ራሱን ሲጐትት፣ፍላጎት ሲጠፋ፤በዚያም ጊዜ ሰው ወደ ዘላለማዊ ቤቱ ይሄዳል፤አልቃሾችም በአደባባዮች ይዞራሉ።
6 የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ፣የወርቅ ሳሕንም ሳይሰበር፣የውሃ መቅጃው በምንጩ አጠገብ ሳይከሰከስ፣ወይም መንኰራኵሩ በውሃ ጒድጓድ ላይ ሳይሰበር፣
7 ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ፣ፈጣሪህን አስብ።
8 ሰባኪው “ከንቱ ከንቱሁሉም ነገር ከንቱ ነው!” ይላል።