1 እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤የሚያጽናናቸውም አልነበረም።
2 እኔም የቀድሞ ሙታን፣ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ደስተኞች እንደሆኑ ተናገርሁ።
3 ነገር ግን ከሁለቱም ይልቅ፣ገና ያልተወለደው፣ከፀሓይ በታች የሚደረገውንም፣ክፋት ያላየው ይሻላል።
4 እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
5 ሰነፍ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል።
6 በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል።
7 ደግሞም ከፀሓይ በታች ከንቱ የሆነን ነገር አየሁ፤