7 ደግሞም ከፀሓይ በታች ከንቱ የሆነን ነገር አየሁ፤
8 ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ብቸኛ ሰው አለ፤ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው?ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበውለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው።
9 ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤
10 አንዱ ቢወድቅ፣ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል።ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣እንዴት አሳዛኝ ነው!
11 ደግሞም ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?
12 አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።
13 ምክርን መቀበል ከማያውቅ ሞኝና ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ጠቢብ የሆነ ድኻ ወጣት ይሻላል።