3 አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሰኘበትና በአግባብ ካል ተቀበረ፣ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤
4 ምክንያቱም በከንቱ ይመጣል፤ በጨለማም ይሄዳል፤ ስሙም በጨለማ ተሸፍኖአል።
5 ፀሓይን ባያይና ምንም ነገር ባያውቅ እንኳ፣ እርሱ ከዚያ ሰው ይልቅ ዕረፍት አለው፤
6 ሁለት ጊዜ ሺህ ዓመት ቢኖር ነገር ግን በሀብቱ ደስ ባይሰኝበት ሁሉ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድ አይደለምን?
7 የሰው ጥረት ሁሉ ለአፉ ነው፤ፍላጎቱ ግን ፈጽሞ አይረካም።
8 ጠቢብ ከሞኝ ይልቅ ምን ብልጫ አለው?ድኻስ በሌሎች ፊት እንዴት እንደሚኖር በማወቁ፣ትርፉ ምንድን ነው?
9 በምኞት ከመቅበዝበዝ፣በዐይን ማየት ይሻላል፤ይህም ደግሞ ከንቱ፣ነፋስንም እንደ መከተል ነው።