24 ጥበብ ምንም ይሁን ምን፣እጅግ ጥልቅና ሩቅ ነው፤ማንስ ሊደርስበት ይችላል?
25 ስለዚህ ጥበብንና የነገሮችን አሠራር ለመመርመርና ለማጥናት፣የክፋትን መጥፎነት፣የሞኝነትንም እብደት ለማስተዋል፣አእምሮዬን መለስሁ።
26 ልቧ ወጥመድ፣እጆቿም እግር ብረት የሆኑ፣አሽክላ የሆነች፣ከሞት የከፋችዋን ሴት አገኘሁ፤እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ከእጇ ያመልጣል፤ኀጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
27 ሰባኪው እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ መርምሬ ያገኘሁት ነገር ይህ ነው፤“የነገሮችን ብልኀት መርምሮ ለማግኘት፣አንዱን በአንዱ ላይ በመጨመር፣
28 ገና በመመርመር ላይ ሳለሁ፣ግን ያላገኘሁት፣ከሺህ ወንዶች መካከል አንድ ቅን ሰው አገኘሁ፣በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ቅን ሴት አላገኘሁም።