መክብብ 9:7-13 NASV

7 ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር እግዚአብሔር ደስ ብሎታልና።

8 ዘወትር ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘወትር በዘይት ቅባ።

9 እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጒም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።

10 እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።

11 ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፡ሩጫ ለፈጣኖች፣ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤እንጀራ ለጥበበኞች፣ወይም ባለጠግነት ለብልሆች፣ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12 ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

13 እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፦