1 ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው!ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።
2 ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤የሰውን ቤት፣የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።
3 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም።ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።
4 በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤በሐዘን እንጒርጒሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤የወገኔ ርስት ተከፋፍሎአል።ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’
5 ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።