ሚክያስ 3:5-11 NASV

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሕዝቤን የሚያስቱ ነቢያት፣ሰው ሲያበላቸው፣ ‘ሰላም አለ’ ይላሉ፤ሳያበላቸው ሲቀር ግን፣ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።

6 ስለዚህ ሌሊቱ ያለ ራእይ፣ጨለማውም ያለ ንግርት ይመጣባችኋል፤በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች፤ቀኑም ይጨልምባቸዋል።

7 ባለ ራእዮች ያፍራሉ፤ንግርተኞችም ይዋረዳሉ፤ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፤ከእግዚአብሔር መልስ የለምና።”

8 እኔ ግን፣ለያዕቆብ በደሉን፣ለእስራኤልም ኀጢአቱን እነግር ዘንድኀይልን፣ በእግዚአብሔር መንፈስ፣ፍትሕና ብርታት ተሞልቻለሁ።

9 እናንት የያዕቆብ ቤት መሪዎች፣እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች፣ፍትሕን የምትንቁ፤ትክክለኛ የሆነውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ፤ ስሙ፤

10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ፣ኢየሩሳሌምን በክፋት የምትገነቡ፤ ስሙ።

11 መሪዎቿ በጒቦ ይፈርዳሉ፤ካህናቷ ለዋጋ ሲሉ ያስተምራሉ፤ነቢያቷም ለገንዘብ ሲሉ ይናገራሉ።ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ ተደግፈውም፣“እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን?ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይደርስብንም” ይላሉ።