ሚክያስ 5:1-7 NASV

1 አንቺ የጭፍሮች ከተማ ሆይ፤ጭፍሮችሽን አሰልፊ፤ከበባ ተደርጎብናልና፤የእስራኤልን ገዥ፣ጒንጩን በበትር ይመቱታል።

2 “አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣አመጣጡ ከጥንት፣ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣የእስራኤል ገዥ፣ከአንቺ ይወጣልኛል።”

3 ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣እስራኤል ትተዋለች፤የተቀሩት ወንድሞቹም፣ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

4 በእግዚአብሔር ኀይልበአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ተደላድለው ይኖራሉ።

5 እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ሰባት እረኞችን፣እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

6 የአሦርን ምድር በሰይፍ፣የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤አሦራዊው ምድራችንን ሲወር፣ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣እርሱ ነጻ ያወጣናል።

7 የያዕቆብ ትሩፍ፣በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ሰውን እንደማይጠብቅ፣የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።