ሚክያስ 5:3-9 NASV

3 ስለዚህ ወላዲቱ አምጣ እስክትገላገል ድረስ፣እስራኤል ትተዋለች፤የተቀሩት ወንድሞቹም፣ተመልሰው ከእስራኤላውያን ጋር ይቀላቀላሉ።

4 በእግዚአብሔር ኀይልበአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ታላቅነት፣ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል።በዚያን ጊዜ ኀያልነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ፣ተደላድለው ይኖራሉ።

5 እርሱም ሰላማቸው ይሆናል።አሦራዊ ምድራችንን ሲወር፣ምሽጐቻችንንም ጥሶ ሲገባ፣ሰባት እረኞችን፣እንዲያውም ስምንት አለቆችን እናስነሣበታለን።

6 የአሦርን ምድር በሰይፍ፣የናምሩድን ምድር በተመዘዘ ሰይፍ ይገዛሉ፤አሦራዊው ምድራችንን ሲወር፣ዳር ድንበራችንን ሲደፍር፣እርሱ ነጻ ያወጣናል።

7 የያዕቆብ ትሩፍ፣በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ሰውን እንደማይጠብቅ፣የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።

8 በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በእግሩ እየጨፈላለቀ እንደሚሄድ፣የሰበረውን ማንም ሊነጥቀው እንደማይችል፣በበግ መንጋ መካከል እንዳለ፣እንደ ደቦል አንበሳ ሁሉ፣የያዕቆብም ትሩፍ፣ በአሕዛብ ዘንድ፣ በብዙም ሕዝብ መካከል እንደዚሁ ይሆናል።

9 እጅህ በጠላቶችህ ላይ በድል አድራጊነት ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይጠፋሉ።