ሶፎንያስ 1:10-16 NASV

10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን ‘ከዓሣ በር’ ጩኸትበሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ከኰረብቶችም ታላቅ ሽብር ይሰማል።

11 እናንት በመክቴሽ ገበያ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ነጋዴዎቻችሁ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይሞታሉ።

12 በዚያ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ተንደላቀው የሚኖሩትን፣በዝቃጩ ላይ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትን፣‘ክፉም ይሁን መልካም፣ እግዚአብሔር ምንም አያደርግም’ የሚሉትን ቸልተኞች እቀጣለሁ።

13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ቤታቸው ይፈራርሳል፤ቤቶች ይሠራሉ፤ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ወይን ይተክላሉ፤ጠጁን ግን አይጠጡም።

14 “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤

15 ያ ቀን የመዓት ቀን፣የመከራና የጭንቀት ቀን፣የሁከትና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤

16 ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣በረጃጅም ግንቦች ላይ፣የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።