15 ያ ቀን የመዓት ቀን፣የመከራና የጭንቀት ቀን፣የሁከትና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤
16 ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣በረጃጅም ግንቦች ላይ፣የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።
17 እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና።ደማቸው እንደ ትቢያ፣ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።
18 በእግዚአብሔር የቊጣ ቀን፣ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው፣ሊያድናቸው አይችልም፤መላዪቱ ምድር፣በቅናቱ ትበላለች፤በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና።”