11 እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክትሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
12 “ኢትዮጵያውያን ሆይ፤ እናንተም፣በሰይፌ ትገደላላችሁ።”
13 እጁን በሰሜን ላይ ይዘረጋል፤አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌን ፍጹም ባድማ፣እንደ ምድረ በዳም ደረቅ ያደርጋታል።
14 የበግና የከብት መንጋዎች፣የፍጥረት ዐይነት ሁሉ በውስጧ ይመሰጋሉ፤ጒጒትና ጃርት፣በግንቦቿ ላይ ያድራሉ።ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ፍርስራሽ በየደጃፉ ይከመራል፤ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይገለጣሉ።
15 ተዘልላ የኖረች፣ደስተኛዪቱ ከተማ ይህች ናት፤እርሷም በልቧ፣“እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም” ያለች፣ታዲያ እንዴት የዱር አራዊት የሚመሰጉባት፣ባድማ ሆና ቀረች?በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ፣ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል።