7 ምሽጎቿን እንዲበላ፣በጋዛ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።
8 በአስቀሎና በትር የያዘውን፣የአሸዶድንም ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰውእስኪሞት ድረስ፣እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤”ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም።የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
10 ምሽጎችዋን እንዲበላ፣በጢሮስ ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”
11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ርኅራኄን በመንፈግ፣ወንድሙን በሰይፍ አሳዶታልና፤የቊጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤
12 የባሶራን ምሽጎች እንዲበላ፣በቴማን ቅጥሮች ላይ እሳት እሰዳለሁ።”
13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የአሞን ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ድንበሩን ለማስፋት፣የገለዓድን ነፍሰ ጡር ሴቶች ሆድ ቀዶአልና።