አሞጽ

ምዕራፎች 2:4-10

መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የይሁዳ ኀጢአት፣ይልቁን ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋል፤ትእዛዙንም አልጠበቁምና፤አባቶቻቸው በተከተሏቸው አማልክት፣በሐሰት አማልክት በመመራት ስተዋልና። 5የኢየሩሳሌምን ምሽጎች እንዲበላ፣በይሁዳ ላይ እሳት እሰዳለሁ። 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የእስራኤል ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ጻድቁን ስለ ጥሬ ብር፣ችግረኛውንም ስለ ጥንድ ጫማ ይሸጡታልና። 7የድኾችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይይረግጣሉ፤ፍትሕንም ከጭቊኖች ይነጥቃሉ፤አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋር ይተኛሉ፤እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ። 8በመያዣነት በተወሰደው ልብስ ላይ፣በየመሠዊያው ሥር ይተኛሉ፤በአምላካቸው ቤት፣በመቀጫነት የተወሰደውን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ። 9ቁመቱ እንደ ዝግባ፣ጥንካሬውም እንደ ባሉጥ ዛፍ የነበረ ቢሆንም፣አሞራዊውን ከፊታቸው አጠፋሁት፣ከላይ ፍሬውን፣ከታችም ሥሩን አጠፋሁ። 10“የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣ከግብፅ አወጣኋችሁ፤አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።