አሞጽ 6:6-12 NASV

6 በፋጋ የወይን ጠጅ ለምትጠጡ፣ምርጥ ሽቱም ለምትቀቡ፣ስለ ዮሴፍ መከራ ግን ለማታዝኑ ወዮላችሁ!

7 ስለዚህ እናንተ በመጀመሪያ በምርኮ ከሚወሰዱት መካከል ናቸሁ፤መፈንጠዛችሁና መዝናናታችሁም ያበቃል።

8 ጌታእግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ከተማዪቱንና በውስጥዋ ያለውን ሁሉ፣አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል፤ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።

9 በአንድ ቤት ውስጥ ዐሥር ሰዎች ቢቀሩ እነርሱም ይሞታሉ።

10 በድኖቹንም ከቤት አውጥቶ ማቃጠል ያለበት አንድ ዘመድ መጥቶ ተደብቆ ያለውን ሰው፣ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ሲለው፣ እርሱም “የለም” ይለዋል፤ ከዚያም በኋላ፣ “ዝም በል፤ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አይገባንም” ይለዋል።

11 እነሆ፤ እግዚአብሔር ትእዛዝ ሰጥቶአልና፤ታላላቅ ቤቶችን ያወድማቸዋል፤ትንንሾቹንም ያደቅቃቸዋል።

12 ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን?ሰውስ እዚያ ላይ በበሬ ያርሳልን?እናንተ ግን ፍትሕን ወደ መርዝነት፣የጽድቅንም ፍሬ ወደ መራራነት ለወጣችሁ።