ኢዩኤል 2:21-27 NASV

21 ምድር ሆይ፤ አትፍሪ፤ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤በእርግጥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአል።

22 የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ዛፎቹ ፍሬያቸውን አፍርተዋል፤የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።

23 የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤በአምላካችሁ በእግዚአብሔር፣ ሐሤት አድርጉ፤የበልግን ዝናብ፣በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፤እንደ ቀድሞውም፣የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል።

24 ዐውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤መጥመቂያ ጒድጓዶችም፣ በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈሳሉ።

25 “በመካከላችሁ የሰደድሁት ታላቁ ሰራዊት፣ትልልቁ አንበጣና ትንንሹ አንበጣ፣ሌሎች አንበጦችና የአንበጣው መንጋ የበላውን፣እነዚህ ሁሉ የበሏቸውን ዓመታት ዋጋ እመልስላችኋለሁ።

26 እስክትጠግቡ የምትበሉት ብዙ ምግብ ይኖራችኋል፤ድንቅ ነገሮችን ለእናንተ የሠራውን፣የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።

27 ከዚያም እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፣እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደሆንሁ፣እንደ እኔም ያለ፣ ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም።