ዘካርያስ 10:5-11 NASV

5 ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስለ ሆነ ተዋግተው፤ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።

6 “የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ።ስለምራራላቸው፣ወደቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎችይሆናሉ፤እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ጸሎታቸውን እሰማለሁ።

7 ኤፍሬማውያን እንደ ኀያላን ሰዎች ይሆናሉ፤ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ሐሤት ያደርጋል።ልጆቻቸው ያዩታል፤ ደስተኛም ይሆናሉ፤ልባቸውም በእግዚአብሔር ደስ ይለዋል።

8 በፉጨት እጠራቸዋለሁ፤በአንድነት እሰበስባቸዋለሁ፤በእርግጥ እቤዣቸዋለሁ፤እንደ ቀድሞው ይበዛሉ።

9 በሕዝቦች መካከል ብበትናቸውም፣በሩቅ ምድር ሆነው ያስቡኛል፤እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው፣በሕይወት ይመለሳሉ።

10 ከግብፅ እመልሳቸዋለሁ፤ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም።

11 በመከራ ባሕር ውስጥ ያልፋሉ፤የባሕሩ ማዕበል ጸጥ ይላል፤የዐባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል።የአሦር ትምክሕት ይዋረዳል፤የግብፅም በትረ መንግሥት ያበቃል።