1 ሊባኖስ ሆይ፤ እሳት ዝግባሽን እንዲ በላው፣ደጆችሽን ክፈቺ!
2 የጥድ ዛፍ ሆይ፤ ዝግባ ወድቋልና አልቅስ፤የከበሩትም ዛፎች ጠፍተዋል!የባሳን ወርካዎች ሆይ፤ አልቅሱ፤ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሮአል!
3 የእረኞችን ዋይታ ስሙ፤ክብራቸው ተገፎአልና፤የአንበሶችን ጩኸት ስሙ፤ጥቅጥቅ ያለው የዮርዳኖስ ደን ወድሟል!
4 እግዚአብሔር አምላኬ እንዲህ ይላል፤ “ለዕርድ የተለዩትን በጎች አሰማራ፤
5 የገዟቸው ያርዷቸዋል፤ ሳይቀጡም ይቀራሉ፤ የሸጧቸውም፣ ‘እግዚአብሔር ይመስገን፤ ባለጠጋ ሆኛለሁ’ ይላሉ፤ ጠባቂዎቻቸውም እንኳ አይራሩላቸውም።