6 “ኑ! ኑ! ውጡ ከሰሜን ምድር አምልጡ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለአራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።
7 “አንቺ ጽዮን ነዪ፤ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፤ ኰብልዪ።”
8 እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላልና፤ “ካከበረኝና በዘረፉአችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፣ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፤
9 እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያም እግዚአብሔር ጸባኦት እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
10 “የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ ደስም ይበልሽ፤ እኔ እመጣለሁና፤ በመካከልሽም እኖራለሁ” ይላል እግዚአብሔር።
11 “በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ እግዚአብሔር ጸባኦት ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።
12 እግዚአብሔርም በተቀደሰችው ምድር ይሁዳን ርስቱ አድርጎ ይወርሳል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ይመርጣል።