7 “እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።
8 “ ‘ሊቀ ካህኑ ኢያሱ ሆይ፤ ስማ፤ በፊትህ የሚቀመጡትም ረዳቶችህ ገና ወደ ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፤ ባሪያዬን ቊጥቋጡን አመጣለሁ።
9 በኢያሱ ፊት ያስቀመጥሁት ድንጋይ እነሆ! በዚያ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ፤’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።
10 “ ‘በዚያን ቀን እያንዳንዱ በገዛ ወይኑና በለሱ ሥር ሆኖ ባልንጀራውን ይጋብዛል፤’ ” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።