3 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚወጣ ርግማን ነው፤ በአንደኛው በኩል እንደ ተጻፈው የሚሰርቅ ሁሉ ይጠፋል፤ በሌላው በኩል ደግሞ እንደ ተጻፈው በሐሰት የሚምል ሁሉ ይጠፋልና።
4 እግዚአብሔር ጸባኦት ‘እኔ ርግማኑን አመጣዋለሁ፤ እርሱም ወደ ሌባው ቤትና በስሜ በሐሰት ወደሚምለው ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ይቀመጣል፤ ቤቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል ይላል።”
5 ከዚያም ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደ ላይ ተመልከት፤ ይህ የሚመጣው ምን እንደሆነ እይ” አለኝ።
6 እኔም፣ “ምንድን ነው?” አልሁት። እርሱም፣ “የኢፍ መስፈሪያ ነው” አለኝ። ቀጥሎም “ይህ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ያለው የሕዝቡ በደል ነው” አለኝ።
7 ከዚያም ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ፤ የኢፍ መስፈሪያ ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር።
8 እርሱም፣ “ይህች ርኵሰት ናት” ብሎ ወደ ኢፍ መስፈሪያ መልሶ አስገባት፤ የእርሳሱንም ክዳን ወደ ቅርጫቱ አፍ ገፍቶ ገጠመው።
9 ከዚያም ወደ ላይ ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ከፊቴ ሁለት ሴቶች ነበሩ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ ክንፎቻቸውም እንደ ሽመላ ክንፎች ነበሩ፤ የኢፍ መስፈሪያውንም በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።