3 እነርሱም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቤት ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደረግሁት፣ በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን?” ብለው ጠየቁ።
4 ከዚያም የእግዚአብሔር ጸባኦት ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
5 “የምድሩን ሕዝብ ሁሉና ካህናቱን እንዲህ በላቸው፤ ‘ባለፉት ሰባ ዓመታት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት በእርግጥ ለእኔ ነበርን?
6 ትበሉና ትጠጡ የነበረውስ ለራሳችሁ አይደለምን?
7 ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ላይ ሳሉ፣ የደቡብና የምዕራብ ኰረብቶች ግርጌ የሰው መኖሪያም በነበሩበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት የተናገረው ቃል ይህ አልነበረምን?’ ”
8 የእግዚአብሔር ቃል እንደ ገና ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፤
9 “እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘እውነተኛ ፍትሕ አስፍኑ፣ እርስ በርሳችሁ ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤