1 የእግዚአብሔር ቃል ንግር በሴድራክ ምድር ላይ ይወርድበታል፤በደማስቆም ላይ ያርፍበታል፤የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ዐይን፣ በእግዚአብሔር ላይ ዐርፎአልና።
2 ደግሞም በአዋሳኟ በሐማት፣ጥበበኞች ቢሆኑም እንኳ በጢሮስና በሲዶና ላይ ያርፍባቸዋል።
3 ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ብሩን እንደ ዐፈርወርቁንም እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቈልላለች።
4 ጌታ ግን ሀብቷን ይወስዳል፤በባሕር ያላትንም ኀይል ይደምስሳል፤እርሷም በእሳት ፈጽማ ትጠፋለች።