ዘካርያስ 9:12-17 NASV

12 እናንት በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች፤ ወደ ምሽጎቻችሁ ተመለሱ፤አሁንም ቢሆን ሁለት ዕጥፍ አድርጌ እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ።

13 ቀስቴን እንደ ገተርሁ፣ ይሁዳን እገትረዋለሁ፤ኤፍሬምንም ፍላጻ አደርገዋለሁ፤ጽዮን ሆይ፤ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ግሪክ ሆይ፤ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ።

14 እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይገለጣል፤ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይወጣል፤ጌታ እግዚአብሔር መለከት ይነፋል፤በደቡብም ዐውሎ ንፋስ ውስጥ ይጓዛል፤

15 እግዚአብሔር ጸባኦትም ይከልላቸዋል፤ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ፤ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤የመሠዊያውን ማእዘኖች ለመርጨት፣እንደ ተዘጋጀ ዕቃ፣ እነርሱም እንደዚሁ ተሞልተዋል።

16 ሕዝቡን የራሱ መንጋ አድርጎበዚያ ቀን አምላካቸው እግዚአብሔር ያድናቸዋል።በአክሊል ላይ እንዳለ ዕንቍ፣በገዛ ምድሩ ላይ ያብለጨልጫሉ።

17 እንዴት ውብና አስደናቂ ይሆናሉ፤እህል ጎልማሶችን፣አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅትን ያሳምራል።