ዘዳግም 12:22-28 NASV

22 ሚዳቋ ወይም ድኵላ እንደሚበላ አድርገህ ብላ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆኑትና ያልሆኑት ሊበሉ ይችላሉ።

23 ደሙን ግን እንዳትበላ ተጠንቀቅ፤ ደም ሕይወት ስለ ሆነ፣ ሥጋን ከነሕይወቱ አትብላ።

24 ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።

25 በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላቸው አትብላው።

26 ነገር ግን የተቀደሱ ነገሮችህን ለመስጠት የተሳልሃቸውን ሁሉ ይዘህ እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።

27 የሚቃጠል መሥዋዕትህን፣ ሥጋውንም ደሙንም በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ላይ አቅርብ። የመሥዋዕትህ ደም በአምላክህበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፤ ሥጋውን ግን መብላት ትችላለህ።

28 በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት መልካምና ትክክል የሆነውን ነገር ስለምታደርግ፣ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ ለዘላለም መልካም እንዲሆንላችሁ፣ እኔ የምሰጥህን እነዚህን ደንቦች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽማቸው።