ዘዳግም 21:10-16 NASV

10 ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ልትገጥም ወጥተህ አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) እነርሱን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶህ በማረክህ ጊዜ፣

11 ከምርኮኞቹ መካከል መልከ መልካም ሴት አይተህ ብትማርክህ፣ ሚስትህ ልታደርጋት ትችላለህ።

12 ወደ ቤትህ ውሰዳት፤ ጠጒሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቍረጥ።

13 ስትማረክ የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፤ እቤትህ ተቀምጣ ለአባትና ለእናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፣ ልትደርስባትና ባል ልትሆናት፣ እርሷም ሚስት ልትሆንህ ትችላለች።

14 በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፣ ወደምትፈልገው አንድትሄድ ነጻነት ስጣት፤ ውርደት ላይ ጥለሃታልና ልትሸጣት ወይም እንደ ባሪያ ልትቈጥራት አይገባህም።

15 አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፤ አንደኛዋን የሚወዳት፣ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት በኵር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፣

16 ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፣ የብኵርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኵር ልጅ ገፎ፣ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ፣ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤