ዘዳግም 21:3-9 NASV

3 ከዚያም ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፣

4 ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን ዐንገት ይስበሩ፤

5 እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር (ያህዌ) ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጒዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።

6 ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ባለችው ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፣ በሸለቆው ውስጥ፣ ዐንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ።

7 እንዲህም ብለው ይናገሩ፤ “እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም።

8 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።” ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል።

9 አንተም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ቀና የሆነውን ስታደርግ፣ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከልህ ታስወግዳለህ።