3 በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ በአምላክህበእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ፊት እናገራለሁ” በለው።
4 ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ፣ በአምላክህ በእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል።
5 አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሂም) ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፤ “አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፣ ኀያልና ቊጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።
6 ግብፃውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም።
7 ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ (ያህዌ) ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጒስቊልናችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ።
8 ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር (ያህዌ) በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን።
9 ወደዚህ ስፍራ አመጣን፤ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን፤