22 በቊጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል።ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።
23 “በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ።ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
24 የሚያጠፋ ራብ፣ በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድመቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤የአራዊትን ሹል ጥርስ፣ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝምእሰድባቸዋለሁ።
25 ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ቤታቸውም ውስጥ ድንጋጤ ይነግሣል፤ጐልማሳውና ልጃገረዷ፣ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ።
26 እበትናቸዋለሁ፤ ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውንአጠፋለሁ አልሁ፤
27 ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፣‘ድል ያደረገችው እጃችን እንጂ፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፣’ ”የጠላትን መነሣሣት ሠጋሁ።
28 አእምሮ የጐደላቸው፣ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው።