29 አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡ፣መጨረሻቸውም ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነበር።
30 መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ካልተዋቸው በቀር፣አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል?ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደርጋሉ?
31 የእነርሱ መጠጊያ ዐለት እንደ እኛ መጠጊያዐለት አይደለምና፤ ጠላቶቻችንም እንኳ ይህን አይክዱም።
32 ወይናቸው ከሰዶም ወይን፣ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፣ዘለላቸውም በምሬት የተሞላ ነው።
33 ወይናቸው የእባብ መርዝ፣የመራዥ እባብም መርዝ ነው።
34 “ይህ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፣በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?
35 በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”