ዘዳግም 33:18-24 NASV

18 ስለ ዛብሎንም እንዲህ አለ፦“ዛብሎን ሆይ፤ ወደ ውጭ በመውጣትህ፣አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ፤

19 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ።በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።”

20 ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦“የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተመሰገነ ነው!ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፣ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።

21 ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ፤የአለቃም ድርሻ ለእርሱ ተጠብቆለታል።የሕዝቡ መሪዎች በተሰበሰቡ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) የቅን ፈቃድና፣በእስራኤል ላይ የበየነውን ፍርዱን ፈጸመ።”

22 ስለ ዳንም እንዲህ አለ፦“ዳን ከባሳን ዘሎ የሚወጣ፣የአንበሳ ደቦል ነው።”

23 ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦“ንፍታሌም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ሞገስ ረክቶአል፤በበረከቱም ተሞልቶአል፤ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።”

24 ስለ አሴርም እንዲህ አለ፦“አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ነው፤በወንድሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።