1 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር እንድትጠብቁት አስተምራችሁ ዘንድ አምላካችሁእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) የሰጠኝ ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ ይህ ነው፤
2 ይኸውም፣ የምሰጣችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ በመጠበቅ፣ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም፣ አንተ፣ ልጆችህና ከእነርሱ በኋላ የሚመጡት ልጆቻቸው በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትፈሩት ዘንድ ነው።
3 እንግዲህ እስራኤል ሆይ ስማ፤ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር መልካም እንዲሆንልህና እጅግ እንድትበዛ፣ ትእዛዙንም ትጠብቅ ዘንድ ጥንቃቄ አድርግ።
4 እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችንእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አንድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
5 አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።