4 እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላካችንእግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) አንድ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነው።
5 አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ ውደድ።
6 ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ።
7 ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።
8 በእጅህ ላይ ምልክት አድርገህ እሰራቸው፤ በግንባርህም ላይ ይሁኑ።
9 በቤትህ መቃኖች በግቢህም በሮች ላይ ጻፋቸው።
10 አምላክህ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣