3 የጋሜር ልጆች፦አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።
4 የያዋን ልጆች፦ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ ናቸው።
5 ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
6 የካም ልጆች፦ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።
7 የኩሽ ልጆች፦ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።የራዕማ ልጆች፦ሳባ፣ ድዳን ናቸው።
8 ኩሽ የናምሩድ አባት ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ።
9 በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።