11 አብርሃም ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይስሐቅን ባረከው፤ በዚህ ጊዜ ይስሐቅ በብኤርላሃይሮኢ አቅራቢያ ይኖር ነበር።
12 ግብፃዊቷ የሣራ አገልጋይ አጋር፣ ለአብርሃም የወለደችለት የእስማኤል ትውልድ ይህ ነው።
13 የእስማኤል ልጆች ስም እንደ ዕድሜያቸው ቅደም ተከተል እንዲህ ነው፦ የእስማኤል በኵር ልጅ ነባዮት፣ ቄዳር፣ ነብዳኤል፣ መብሳም፣
14 ማስማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣
15 ኩዳን፣ ቴማን፣ ኢጡር፣ ናፌስና ቄድማ።
16 እነዚህ የእስማኤል ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም በኖሩባቸውና በሰፈ ሩባቸው ቦታዎች የዐሥራ ሁለት ነገድ አለቆች ስሞች ናቸው።
17 እስማኤል በጠቅላላው መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።