1 ይስሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው።እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።
2 ይስሐቅም እንዲህ አለ፤ “ይኸው እኔ አርጅቻለሁ፤ የምሞትበትንም ቀን ዐላውቅም
3 ስለዚህ የአደን መሣሪያህን፦ የፍላጻ ኰሮጆህንና ቀስትህን ይዘህ ወደ ዱር ሂድ፤ አድነህም አምጣልኝ።
4 ከመሞቴ በፊት እንድመርቅህ የምወደውን ዐይነት ጣዕም ያለው ምግብ አዘጋጅተህ አብላኝ።”
5 ይስሐቅ ለልጁ የተናገረውን ርብቃ ትሰማ ስለ ነበር፣ ዔሳው የታዘዘውን ለማምጣት ለዐደን እንደ ወጣ፣
6 ርብቃ ለልጇ ለያዕቆብ እንዲህ አለችው፤ “አባትህ ዔሳውን፣