51 ደግሞም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካከል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤
52 ይህን ክምር ድንጋይ አልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት አልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፣ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።
53 የአብርሃም አምላክ፣ የናኮር አምላክ፣ የአባታቸውም አምላክ (ኤሎሂም) በመካከላችን ይፍረድብን”።ስለዚህ ያዕቆብ በአባቱ በይስሐቅ ፍርሀት ማለ።
54 ያዕቆብ በኰረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው አደሩ።
55 በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም፣ ወደ አገሩ ተመለሰ።