1 ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው፦
2 ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣
3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።
4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት።