5 እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
6 ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንሰሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራው ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።
7 ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።
8 ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
9 በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
10 የዔሳው ልጆች ስም፦የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
11 የኤልፋዝ ልጆች፦ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶምና ቄኔዝ፤