1 አዳም ሚስቱን ሔዋንን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ቃየንን ወለደች፤ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ርዳታ ወንድ ልጅ አገኘሁ” አለች።
2 ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።አቤል የበግ እረኛ፣ ቃየንም ዐራሽ ነበር።
3 በአንድ ወቅት፣ ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አቀረበ።
4 አቤልም መጀመሪያ ከተወለዱት በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
5 በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን አልተደሰተም፤ ስለዚህ ቃየን ክፉኛ ተናደደ፤ ፊቱም ጠቈረ።