20 ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ።
21 ወንድሙም ዩባል ይባላል፤ እርሱም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበረ።
22 ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
23 ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤“ዓዳና ጺላ ሆይ ስሙኝ፤የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣ጒልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤
24 ቃየንን የሚገድል ሰባት ጊዜ ቅጣት ካገኘው፣የላሜሕ ገዳይማ ሰባ ሰባት ጊዜ ቅጣት ያገኘዋል።”
25 አዳም እንደ ገና ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር (ያህዌ) ምትክ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ሴት ብላ ጠራችው።
26 ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው።በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም መጥራት ጀመሩ።