10 የስምዖን ልጆች፦ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደውሳኡል ናቸው።
11 የሌዊ ልጆች፦ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።
12 የይሁዳ ልጆች፦ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እናዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናንበከነዓን ምድር ሞቱ።
13 የይሳኮር ልጆች፦ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤
14 የዛብሎን ልጆች፦ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤
15 እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው።
16 የጋድ ልጆች፦ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤