11 አህያውን በወይን ግንድ፣ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ልብሱን በወይን ጠጅ፣መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።
12 ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።
13 “ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።
14 “ይሳኮር፣ ዐጥንተ ብርቱ አህያ፣በጭነት መካከል የሚተኛ፣
15 ማረፊያ ቦታው መልካም፣ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ተገድዶም ያገለግላል።
16 “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።
17 ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።