18 ያሬድ፣ ዕድሜው 162 ዓመት ሲሆን ሄኖክን ወለደ፤
19 ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
20 ያሬድ በአጠቃላይ 962 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
21 ሄኖክ፣ ዕድሜው 65 ዓመት በሆነ ጊዜ ማቱሳላን ወለደ፤
22 ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
23 ሄኖክ በአጠቃላይ 365 ዓመት ኖረ፤
24 ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር (ኤሎሂም) ጋር አደረገ፤ እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ስለ ወሰደውም አልተገኘም።