4 ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ አዳም 800 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤
5 አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
6 ሴት፣ ዕድሜው 105 ዓመት ሲሆን ሄኖስን ወለደ፤
7 ሴት ሄኖስን ከወለደ በኋላ 807 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
8 ሴት በአጠቃላይ 912 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።
9 ሄኖስ፣ ዕድሜው 90 ዓመት በሆነ ጊዜ ቃይናንን ወለደ፤
10 ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።